በአዲስ አበባ ዘንድሮ 181 ሄክታር መሬት መልሶ ይለማል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናችን አዲስ አበባ በያዝነው አመት እጅግ የተጎሳቆሉ ተብለው የተለዩ በ181 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኙ አካባቢዎች መልሰው ሊለሙ ነው።አሮጌው ቄራ፤ ለገሃር፤ አፍሪካ ህብረት ቁጥር ሁለትና ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚገኙ የተጎዱ አካባቢዎች ናቸው ዘንድሮ የመልሶ ማልማቱ ስራ እንደሚከናወንባቸው ፥ የአዲስ አበባ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጄንሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግሯል።
በ2010 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ፈርሰው መልማት ያለባቸው መሆናቸውን ነው ፥ የኤጄንሲው የኮሚዩኒኬሽን ደጋፊ የስራ ሂደት መሪ አቶ ማርቆስ አለማየሁ ከአስር አመት በፊት የተደረገ አንድ የማስተር ፕላን ጥናትን ዋቢ አድርገው የተናገሩት።
እነዚህን የመሰረተ ልማት ያልተሟላላቸውን አካባቢዎች ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት መልሶ የማልማት ስራ መከናወኑንም ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ በዋናነት የሚጠቀሱት የባሻ ወልዴ፣ ሰንጋ ተራ፣ አፍሪካ ህብረት፣ አራት ኪሎ፣ ሸራተንና ኢ ሲ ኤ አካባቢ የነበሩ ቤቶች ፈርሰው ለተለያዩ መንግስታዊና የግል ባለሃብቶች የተሰጠበትና መልሰው እንዲለሙ የተደረገበት ሁኔታ እንዳለም ነው አቶ ማርቆስ የገለጹት።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በበኩሉ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ የተጎዱ አካባቢዎችን በዘመናዊ መልኩ በመቀየር መልካም ገፅታ ለማላበስ የሚያስችል ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።
እስከ 2007 በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የተጎዱና የተጨናነቁ አካባቢዎችን በ40 በመቶ በመቀነስ መልካም ገፅታ በማላበስ የተሟላ የመሰረተ ልማት እንዲኖራቸው ይደረጋል መባሉን ኤልሳቤጥ ካሳ ዘግባለች።
ዜና (ሬዲዮ)
የዜና ትንታኔዎችና ሀተታ
የቀደሙት የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉ...
1ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን የተካሄደው ይህ ጉባኤ ጥር 1983 ዓ.ም ላይ ነበር። በዚህ ጉባኤ የደርግን ወታደራዊ ስርአት ውድቀት ለማፋጠን የትጥቅ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ ተላልፏል። ...
Hits:2129
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አዲስ...
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ/ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡ 1. ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል 2. አቶ አባይ ወልዱ 3. ወ/ሮ አዜብ መስፍን 4. አቶ አባይ ፅሃየ 5. ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም 6. ወ/ሮ ፈ...
Hits:5496
በኢትዮጵያ የብሔራዊ ኢኮኖሚ አካ...
አዲስ አበባ ፣ ጥር 27፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገሪቱን ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚለካ አዲስ የብሔራዊ ኢኮኖሚ አካውንት መረጃዎች ቋሚ ዓመት ለውጥ መደረጉን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ። በ2004 በጀት ዓመ...
Hits:1318

Comments